በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዮርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤
ኢያሱ 18:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደቡብም ዳርቻ የሚጀምረው ከቂርያት-ይዓሪም ዳርቻ አጠገብ ነበረ፤ ድንበሩም በምዕራቡ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስተ ደቡብ ያለው ድንበር ደግሞ በምዕራብ በኩል ከቂርያትይዓይሪም ጥግ ይነሣና እስከ ኔፍቶ ውሃ ምንጭ ይዘልቃል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደቡቡም ድንበር በምዕራብ በኩል ከቂርያትይዓሪም መጨረሻ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ውሃ ምንጮች ያልፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የደቡብም ዳርቻ ከቅርያታርም መጨረሻ ነበረ፤ ድንበሩም በጋሲን ላይ ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደቡብም ዳርቻ ከቂርያትይዓሪም መጨረሻ ነበረ፥ ድንበሩም በምዕራቡ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ። |
በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዮርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤
ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤
ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፤ መጨረሻውም ቂርያት-ይዓሪም በምትባል በቂርያትበኣል በይሁዳ ልጆች ከተማ ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።