እርሱም “ጌታ ሆይ! አምናለሁ፤” አለ፤ ሰገደለትም።
ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፤ አምናለሁ” አለ፤ ሰገደለትም።
እርሱም “ጌታ ሆይ! አምናለሁ” ብሎ ሰገደለት።
እርሱም፥ “አቤቱ፥ አምናለሁ” ብሎ ሰገደለት።
እርሱም፦ “ጌታ ሆይ፥ አምናለሁ” አለ፤ ሰገደለትም።
ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።
ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፥ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፥
በጀልባዋ የነበሩትም “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።
ባዩትም ጊዜ ሰገዱ፤ አንዳዶቹ ግን ተጠራጠሩ።
እነሆ ኢየሱስ አገኛቸውና “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።
እነሆ አንድ ለምጻም መጥቶ ሰገደለትና “ጌታ ሆይ! ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” አለው።
እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤
ቶማስም “ጌታዬና አምላኬ!” ብሎ መለሰለት።
ኢየሱስም “የማያዩ እንዲያዩ የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጣሁ፤” አለ።