ዮሐንስ 9:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም የተነሣ ዐይነ ሥውሩን፥ “አንተ ዐይኖችህን ስለ ከፈተ፥ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም “ነቢይ ነው፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ ዐይነ ስውር ወደ ነበረው ሰው ተመልሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው፣ እንግዲህ አንተ ምን ትላለህ?” አሉት። ሰውየውም፣ “እርሱ ነቢይ ነው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ዕውር የነበረውን ሰው፥ “አንተስ ዐይኖችህን አበራልኝ ስለምትለው ስለዚያ ሰው ምን ትላለህ?” ሲሉ ደግመው ጠየቁት። እርሱም “ነቢይ ነው!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም ዕዉሩን፥ “አንተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ? ዐይኖችህን ከፍቶልሃልና” አሉት፤ እርሱም፥ “ነቢይ ነው” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። ከዚህም የተነሣ ዕውሩን፦ “አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም፦ “ነቢይ ነው” አለ። |
እርሱም “ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ ነው፤
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁት፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤