La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 9:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ፈሪሳውያን እንዴት እንዳየ እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ጭቃ በዐይኖቼ አኖረ፤ ታጠብሁም፤ አያለሁም፤” አላቸውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ፈሪሳውያንም እንዴት ማየት እንደ ቻለ ጠየቁት። ሰውየውም፣ “እርሱ ዐይኔን ጭቃ ቀባኝ፤ እኔም ታጠብሁ፤ ይኸው አያለሁ” አላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፈሪሳውያን “እንዴት ማየት ቻልክ?” ብለው ሰውየውን እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ዐይኖቼ ላይ ጭቃ አደረገልኝና ታጠብኩ፤ ከዚያም በኋላ ማየት ቻልኩ” አለ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እን​ዴት እን​ዳየ ዳግ​መኛ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ በዐ​ይ​ኖች አኖ​ረው፥ ታጥ​ቤም አየሁ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ ፈሪሳውያን ደግሞ እንዴት እንዳየ እንደ ገና ጠየቁት። እርሱም፦ “ጭቃ በዓይኖቼ አኖረ ታጠብሁም አያለሁም” አላቸውም።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 9:15
4 Referencias Cruzadas  

ባሮክንም፦ “እነዚህን ሁሉ ቃላት እንዴት እንደ ጻፍከው እስኪ ንገረን፤ እርሱ እየነገረህ ነውን?” ብለው ጠየቁት።


ከዚህም የተነሣ ዐይነ ሥውሩን፥ “አንተ ዐይኖችህን ስለ ከፈተ፥ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም “ነቢይ ነው፤” አለ።