ሁሉም ነገር በአባቴ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅደው በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
ዮሐንስ 7:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ፤ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ፤” ብሎ ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን ከርሱ ዘንድ ስለ ሆንሁ፣ እርሱም ስለ ላከኝ ዐውቀዋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ስለ መጣሁና እርሱ ስለ ላከኝ ዐውቀዋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን አውቀዋለሁ፤ እኔ ከእርሱ ነኝና፥ እርሱም ልኮኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ” ብሎ ጮኸ። |
ሁሉም ነገር በአባቴ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅደው በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
ነገር ግን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን አውቀዋለሁ። አላውቀውም ብል ኖሮ እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንሁ ነበር፤ ዳሩ ግን አውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።