ዮሐንስ 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድም “ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል?” ብለው ይደነቁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም በመደነቅ፣ “ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ሊያውቅ ቻለ?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አይሁድም፥ “ይህ ሰው ሳይማር ይህን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ቻለ?” እያሉ ይደነቁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም፥ “ይህ ሳይማር መጽሐፍን እንዴት ያውቃል?” እያሉ ትምህርቱን አደነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድም፦ “ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል?” ብለው ይደነቁ ነበር። |
ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፤ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤
ቀድሞ የሚያውቁት ሁሉ ከነቢያቱ ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው፥ “የቂስን ልጅ ምን ነካው? ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” ሲሉ ተጠያየቁ።