La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 6:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፊልጶስ “እያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ እንኳ እንዲቀበሉ የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም፤” ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፊልጶስም፣ “እያንዳንዱ ሰው ትንሽ ትንሽ እንዲቃመስ ለማድረግ፣ የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ እንኳ አይበቃም” ሲል መለሰ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፊልጶስም “ለእያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ ቊራሽ እንኳ እንዲሰጣቸው የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፊል​ጶ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጥቂት ጥቂት ይወ​ስዱ ዘንድ የሁ​ለት መቶ ዲናር እን​ጀራ አይ​በ​ቃ​ቸ​ውም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፊልጶስ፦ እያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ እንኳ እንዲቀበሉ የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 6:7
10 Referencias Cruzadas  

አገልጋዩ ግን “ይህ ለመቶ ሰው የሚበቃ ይመስልሃልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “እንዲበሉ አቅርብላቸው፤ በልተው መጥገብ ብቻ ሳይሆን እንደሚተርፋቸውም እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለው።


ነገር ግን ያ ባርያ ከዚያ ወጥቶ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን ከባልንጀሮቹ ባርያዎች አንዱን አገኘና ‘ዕዳህን ክፈለኝ’ ብሎ አንቆ ያዘው።


እርሱ ግን መልሶ፥ “የሚበሉትን እናንተው ስጧቸው” አላቸው። እነርሱም፥ “ሄደን በሁለት መቶ ዲናር እንጀራ ገዝተን የሚበሉትን እንስጣቸውን?” አሉት።


በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አገኘውና “ተከተለኝ” አለው።


ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ።


ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ “ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል፤” አለው።


ናትናኤልም “ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን?” አለው። ፊልጶስ “መጥተህ እይ” አለው።


ናትናኤልም “እንዴት አወቅኸኝ?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ ዛፍ ሥር ሆነህ፥ አየሁህ፤” አለው።


“ይህ ሽቶ ለሦስት መቶ ዲናር ተሽጦ ለድሆች ለምን አልተሰጠም?” አለ።