ዮሐንስ 6:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድም “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ፤” በማለቱ ማንጐራጐር ጀመሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም፣ “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ” በማለቱ ያጕረመርሙበት ጀመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኢየሱስ “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ” በማለቱ አይሁድ በእርሱ ላይ አጒረመረሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም ስለ እርሱ አንጐራጐሩ፤ “ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ” ብሎአቸዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አይሁድ፦ ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ ስላለ ስለ እርሱ አንጐራጐሩና፦ |
ከሰማይ የወረደው እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ በልተው ነገር ግን እንደሞቱበት ዓይነት አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል።”
በሕዝቡም መካከል በእርሱ ምክንያት ብዙ ማንጐራጐር ነበረ፤ አንዳንዶቹ “ደግ ሰው ነው፤” ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ ሕዝቡን ያስታል እንጂ፤” ይሉ ነበር።