ዮሐንስ 13:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ስለምን ይህን እንዳለው በማእድ ከተቀመጡት ማንም አላወቀም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ኢየሱስ ለምን እንዲህ እንዳለው ማንም አላወቀም ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ስለምን ይህን እንዳለ በማእድ ከተቀመጡት ማንም የገባው የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብረውትም በማዕድ የተቀመጡት ስለ ምን ይህን እንዳለው አላወቁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከተቀመጡት ስለ ምን ይህን እንዳለው ማንም አላወቀም፤ |
ይሁዳ የገንዘብ ከረጢቱን ይዞ ስለ ነበር፥ አንዳንዶቹ ኢየሱስ “ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ፤ ወይም ለድሆች ምጽዋት ስጥ” ያለው መስሎአቸው ነበርና።