ኢዮብ 8:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፀሐይም ትኩሳት በፊት እርጥብ ነው፥ ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃ እንደ ጠገበ ተክል፣ ፀሓይ እየሞቀው፣ ቅርንጫፉን ሁሉ በአትክልቱ ስፍራ ላይ ይዘረጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አረም በፀሐይ አቈጥቊጦ በአትክልት ቦታው እንደሚበዛ ክፉ ሰዎችም እንደዚሁ ይበዛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፀሐይ በታች ይሻግታል፤ ጫፉም በአትክልት ቦታ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይም ሳይተኵስ ይለመልማል፥ ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል። |
ጌታ ስምሽን፦ “በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ” ብሎ ጠራው፤ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል።