ኢዮብ 5:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፥ የጥፋት አደጋ ሲመጣም አትፈራም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፤ ጥፋት ሲመጣም አትፈራም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከክፉ ምላስ ይጠብቅሃል፤ ጥፋት ቢመጣብህም አትፈራም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምላስ ጅራፍ ይሰውርሃል፥ ከምትመጣብህም ክፋት አትፈራም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፥ ጥፋትም ሲመጣ አትፈራም። |
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።
እነርሱም፦ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ ሤራን እናሢር። ኑ፥ በአንደበት እንምታው፥ ቃላቱንም ሁሉ አናድምጥ” አሉ።