አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥ በዋሾቻቸውም ይቀመጣሉ።
እንስሳት ይጠለላሉ፤ በየዋሻቸውም ይቈያሉ።
በዚያን ጊዜ የዱር አውሬዎች ሸሽተው ወደየመሸሸጊያቸው ይገባሉ፤ በየዋሻቸውም ውስጥ ይሰወራሉ።
አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥ በዋሾቻቸውም ያርፋሉ።
የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮኻሉ፥ ከእግዚአብሔርም ምግባቸውን ይሻሉ።
ፀሐይ ስትወጣ ይሰበሰባሉ፥ በየዋሻቸውም ይተኛሉ።