ኢዮብ 32:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዕድሜ ያረጁ የግድ ጠቢባን አይደሉም፥ ሽማግሌዎችም የግድ ፍርድን አያስተውሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢባን የሚሆኑት በዕድሜ የገፉ ብቻ አይደሉም፤ የሚያስተውሉም ሽማግሌዎች ብቻ አይደሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎችን ጠቢባን የሚያደርጋቸው ሽምግልና አይደለም፤ ትክክለኛውንም ነገር ለማስተዋል የሚረዳቸው የዕድሜ ብዛት አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዕድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም፥ ሽማግሌዎችም ፍርድን አያስተውሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዕድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም፥ ሽማግሌዎችም ፍርድን አያስተውሉም። |
ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እነርሱንም አናግራቸዋለሁ፤ የጌታን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና” አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “የሰማያትና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።