ኢዮብ 32:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ ይልቅ ሽማግሌዎች ነበሩና ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር የሚናገርበትን ጊዜ ይጠባበቅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤሊሁ፣ ሌሎቹ በዕድሜ ይበልጡት ስለ ነበር ከእነርሱ ቀድሞ ለኢዮብ ሳይናገር ቈየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሊሁ በዕድሜ ከሌሎቹ ያነሰ በመሆኑ ሁሉም ተናግረው እስከሚጨርሱ ድረስ በተራው ከኢዮብ ጋር ለመናገር ይጠባበቅ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤሊዩስ ግን ከእርሱ ይልቅ ሽማግሌዎች ነበሩና ለኢዮብ መልስ ለመስጠት ጠብቆ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤሊሁ ግን ከእርሱ ይልቅ ሽማግሌዎች ነበሩና ከኢዮብ ጋር መናገርን ጠብቆ ነበር። |