ቀላይ፦ በእኔ ውስጥ የለችም ይላል፥ ባሕርም፦ በእኔ ዘንድ የለችም ይላል።
ውቅያኖስ፣ ‘በእኔ ውስጥ የለችም’ ይላል፤ ባሕርም፣ ‘በእኔ ዘንድ አይደለችም’ ይላል።
‘ውቅያኖስ በእኔ ውስጥ የለችም’ ይላል፤ ‘ባሕሩም ከእኔ ጋር አይደለችም’ ይላል።
ቀላይ፦ በእኔ ውስጥ የለችም ትላለች። ባሕርም፦ በእኔ ዘንድ የለችም ይላል።
ሰው መንገድዋን አያውቅም፥ በሕያዋን አገር አትገኝም።
በንጹሕ ወርቅ አትገኝም፥ ዋጋዋም በብር አይተመንም።