እንደ ጌታም ቃል የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፦ ‘በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፥ እባክህ፥ ግዛ፤ የርስቱና የመቤዠቱ መብት የአንተ ነውና፤ ለአንተ ግዛው’ አለኝ። ይህም የጌታ ቃል እንደሆነ አወቅሁ።
ኤርምያስ 33:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስ ገና በእስር ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የጌታ ቃል ሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል መጣ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስ በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ በግዞት ሳለ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እርሱ መጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ገና ታስሬ እንዳለሁ የእግዚአብሔር ቃል እንደገና መጣልኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል መጣለት፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል መጣለት፦ |
እንደ ጌታም ቃል የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፦ ‘በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፥ እባክህ፥ ግዛ፤ የርስቱና የመቤዠቱ መብት የአንተ ነውና፤ ለአንተ ግዛው’ አለኝ። ይህም የጌታ ቃል እንደሆነ አወቅሁ።
ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፥ ኤርምያስንም በእስር ቤት አደባባይ አኖሩት፥ እንጀራም ሁሉ ከከተማይቱ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከጋጋሪዎች መንገድ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀምጦ ነበር።