La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 32:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የተገዛበትን የውሉን ሰነድ ከሰጠሁት በኋላ፥ እንዲህ ብዬ ወደ ጌታ ጸለይሁ፦

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የግዥ ውሉን ከሰጠሁ በኋላ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሽያጩን ውል ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ከሰጠሁት በኋላ እኔ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ፦

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለኔ​ርያ ልጅ ለባ​ሮ​ክም የው​ሉን ወረ​ቀት ከሰ​ጠ​ሁት በኋላ፥ እን​ዲህ ብዬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለ​ይሁ፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፥ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፦

Ver Capítulo



ኤርምያስ 32:16
7 Referencias Cruzadas  

አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?


የአጐቴም ልጅ አናምኤል፥ የተገዛበትን የውሉን ሰነድ የፈረሙት ምስክሮች፥ በእስርም ቤት አደባባይ የተቀመጡት አይሁድ ሁሉ እያዩ የተገዛበትን የውሉን ሰነድ ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የኔርያ ልጅ ባሮክ ኤርምያስ በቃል እየነገረው እነዚህን ቃሎች በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።