ያዕቆብ 5:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው ቢኖር የቤተ ክርስቲያን ካህናትን (ሽማግሌዎችን) ወደ እርሱ ይጥራ፤ እነርሱም በሽተኛውን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። |
ንዕማን ግን ተቆጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጉረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር!
ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፤ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ “ጣቢታ ሆይ! ተነሺ፤” አላት። እርሷም ዐይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።