La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ያዕቆብ 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማናቸውም ዓይነት አውሬ፥ አዕዋፍ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡና በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረታት ሁሉ መገራት ችለዋል፤ በሰውም ተገርተዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ማንኛውም ዐይነት እንስሳ፣ አዕዋፍ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡና፣ በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረታት ሁሉ መገራት ችለዋል፤ በሰውም ተገርተዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የምድር አውሬዎችና ወፎች፥ በመሬት የሚሳቡና በባሕር የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ በሰው ሊገሩ ይችላሉ፤ ደግሞም ተገርተዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፤ ደግሞ ተገርቶአል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፥ ደግሞ ተገርቶአል፤

Ver Capítulo



ያዕቆብ 3:7
4 Referencias Cruzadas  

ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ነበር፤ ነገር ግን የእጅ ሰንሰለቱን ይበጥስ፥ የእግር ብረቱንም ይሰብር ነበር። ማንም ይዞ ሊያረጋጋው የሚችል አልነበረም።


በዚያውም አራት እግር ያላቸው ሁሉ አራዊትም በምድርም የሚንቀሳቀሱት የሰማይ ወፎችም ነበሩበት።


ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች።


ነገር ግን ምላስን መግራት የሚችል ማንም ሰው የለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላባትና ዕረፍት የሌላት ክፉ ነገር ናት።