ኢሳይያስ 33:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፍጅት ድምፅ ሕዝቦች ሸሹ፤ በመነሣትህም መንግሥታት ተበተኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፤ መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንተ ድምፅ እንደ መብረቅ በሚበርቅበት ጊዜ ሕዝቦች ይሸሻሉ፤ ከግርማህም የተነሣ መንግሥታት ይበተናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቃልህ ግርማ የተነሣ አሕዛብ ፈርተው ሸሹ፤ አሕዛብም ተበተኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፊጅት ድምፅ ወገኖች ሸሹ፥ በመነሳትህም አህዛብ ተበተኑ። |
ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ቃላት በእነርሱ ላይ ትንቢት ትናገራለህ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ጌታ በላይ ሆኖ ይጮኻል፥ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፤ በበረቱ ላይ እጅግ ይጮኻል፥ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።
ጌታ ከአሕዛብ ጋር ሙግት አለውና ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል ጌታ።