በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
ኢሳይያስ 30:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ስለማይጠቅሟቸው፥ እፍረትና ስድብ እንጂ ረድኤትና ረብ ስለማይሆኗቸው ሕዝቡ ያፍራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውርደትና ኀፍረት ብቻ እንጂ ርዳታም ሆነ ረብ በማያስገኙላቸው፣ ምንም ጥቅም በማይሰጧቸው ሰዎች ምክንያት ሁሉም ለኀፍረት ይዳረጋሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ለእነርሱ ኀፍረትና ውርደት እንጂ ምንም ዐይነት ጥቅምና ርዳታ ሊሰጥ ወደማይችል ሕዝብ መሄድ ለሁሉም አሳፋሪ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላቸው ይጠቅሙአቸው ዘንድ ስለማይችሉ፥ እፍረትና ስድብ እንጂ ረድኤትና ረብ ስለማይሆኑ ሕዝብ ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላቸው ይጠቅሟቸው ዘንድ ስለማይችሉ፥ እፍረትና ስድብ እንጂ ረድኤትና ረብ ስለማይሆኑ ሕዝብ ያፍራሉ። |
በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
ነገር ግን፦ “በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም” አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፦ “በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን” አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዷችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።
እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ የሸንበቆ በትር በግብጽ ተማምነሀል፤ ሰው ተማምኖ ቢመረኰዘው እጁን ወግቶ ያቈስለዋል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርኦን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።