ኢሳይያስ 28:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤ ነገር ግን ለዘለዓለም አይፈጨውም፤ የሠረገላውን መንኰራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቀውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤ ስለዚህ አንድ ሰው ለዘላለም እህል ሲወቃ አይኖርም። የመውቂያውን መንኰራኵር ቢያኼድበትም፣ ፈረሶቹ አይደፈጥጡትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስንዴና ገብስ ይወቃሉ እንጂ እንዲደቁ አይደረጉም፤ ሠረገላና ፈረስ በላያቸው ላይ ቢነዱም እንኳ እንዲደቁ አይደረጉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ለዘለዓለም በእናንተ ላይ አልቈጣም፤ የምሕረቴም ድምፅ አያጠፋችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንጀራ እህል ይደቅቃልን? ለዘላለም አያኬደውም፥ የሰረገላውን መንኮራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቅቀውም። |
“እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ እህልም በወንፊት እንደሚነፋ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
መባቸውንም በጌታ ፊት አመጡ፥ የተሸፈኑ ስድስት ሰረገሎች ዐሥራ ሁለትም በሬዎች፤ ለሁለትም አለቆች ለእያንዳንዳቸው አንድ ሠረገላ ለእያንዳንዱም አለቃ አንዳንድ በሬ አመጡ፤ በማደሪያው ፊት አቀረቡ።