ኢሳይያስ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የሰዶም ገዦች፤ የጌታን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሰዎች፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የሰዶም ገዦች፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሰዎች፤ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የሰዶም ገዢዎች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ! የአምላካችንን ትምህርት አድምጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የሰዶም አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የሰዶም አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ። |
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
እንዲሁም የእስራኤል ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነውና፥ አሕዛብም ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና ግብጽንና ይሁዳን፥ ኤዶምያስንም፥ የአሞንንም ልጆች፥ ሞአብንም፥ በምድረ በዳም የተቀመጡትን ጠጉራቸውን በዙሪያ የተላጩትን ሁሉ በዚያን ዘመን እቀጣለሁ።”
የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት በሚናገሩ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፥ ከገዛ ልባቸውም ትንቢት የሚናገሩትን እንዲህ በላቸው፦ የጌታን ቃል ስሙ፤
ታላቅ እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር ከአንቺ በስተ ሰሜን የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፥ ታናሽ እኅትሽም ከሴቶች ልጆችዋ ጋር ከአንቺ በስተ ደቡብ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።
እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነበር፤ በእርሷና በሴቶች ልጆቿ ትዕቢት፥ የምግብ ጥጋብ፥ የበለጸገ ምቾት ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።
“የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?” ይላል ጌታ። “እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?
ደግሞም ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን ነበር፥ ገሞራንም በመሰልን ነበር” ብሎ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ነው።