ሆሴዕ 12:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአት በገለዓድ አለ፤ ፈጽመው ከንቱ ናቸው፤ በሬዎችን በጌልገላ ይሠዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልሞች ላይ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሸሸ፤ እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል አገለገለ፤ ዋጋዋንም ለመክፈል በጎችን ጠበቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞ አባታችን ያዕቆብ ወደ መስጴጦምያ ሸሽቶ ሄደ፤ እዚያም ሚስት ለማግኘት ሲል የበጎች እረኛ ሆኖ አገለገለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገለዓድ ባይሆንም እንኳ በጌልጌላ መሥዋዕታቸውን የሚሠዉ አለቆች ስተዋል፤ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድንጋይ ክምር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአት በገለዓድ አለ፥ ፈጽመው ከንቱ ናቸው፥ ወይፈኖች በጌልገላ ይሠዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልም ላይ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ። |
እነዚህን ሃያ ዓመታት በአንተ ቤት ነበርሁ፥ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ፥ ስድስት ዓመትም ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።
አንተ ብታመነዝር እንኳ እስራኤል ሆይ! ይሁዳ በደለኛ አይሁን፤ እናንተም ወደ ጌልገላ አትግቡ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፥ ወይም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ!” ብላችሁም አትማሉ።
አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።