ዕብራውያን 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉ፤ ንግግራቸውንም በመሐላ በማጽናት የክርክር ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጥ ይምላሉ፤ መሐላውም የተባለውን ነገር ስለሚያጸና በመካከላቸው የተነሣው ክርክር ሁሉ ይወገዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ሲምሉ ከራሳቸው በሚበልጥ ስም ይምላሉ፤ ንግግራቸውንም በመሐላ በማጽናት በመካከላቸው ያለውን ክርክር ሁሉ ያስወግዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ግን ከእርሱ በሚበልጠው ይምላል፤ የክርክርም መነሻው በመሐላ ይፈጸማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥ ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤ |
አሁንም በእኔም በልጄም በልጅ ልጄም ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፥ ነገር ግን ለአንተ ቸርነትን እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ ለተቀመጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ።”
ንጉሡም ገባዖናውያንን ጠርቶ አነጋገራቸው። ገባዖናውያን ከአሞራውያን የተረፉ እንጂ ከእስራኤል ወገን አልነበሩም፤ እስራኤላውያን ሊጠብቋቸው ቢምሉላቸውም፥ ሳኦል ግን ለእስራኤልና ለይሁዳ ካለው ቅናት የተነሣ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋቸው ፈልጎ ነበር፤