ዕብራውያን 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም እንኳ፣ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም እንኳ በተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጅም ቢሆን መከራን ስለ ተቀበለ መታዘዝን ዐወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ |
እኔ ነፍሴን በፈቃዴ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። አሳልፌ ለመስጠት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ ለመውሰድም ሥልጣን አለኝ፤ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።”