ዕብራውያን 13:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! ይህን በጥቂት ቃል የጻፍኩላችሁን የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ የጻፍሁላችሁ መልእክት ዐጭር እንደ መሆኑ፣ የምክር ቃሌን በትዕግሥት እንድትቀበሉ ዐደራ እላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! ይህ የጻፍኩላችሁ መልእክት አጭር ስለ ሆነ ይህን የምክር ቃሌን በትዕግሥት እንድትቀበሉ አጥብቄ እለምናችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ፥ የምክርን ቃል እንድትቀበሉ እመክራችኋለሁ፤ በጥቂት ቃል ጽፌላችኋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ፥ በጥቂት ቃል ጽፌላችኋለሁና። |
ስለዚህ እግዚአብሔር ጥሪውን የሚያቀርበው በእኛ በኩል በመሆኑ፥ እኛ ለክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ስለ ክርስቶስ ሆነን “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን።
እንደ ታማኝ ወንድም በምቆጥረው በስልዋኖስ በኩል፥ ልመክራችሁና ጸንታችሁ የምትቆሙበት ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልገልጽላችሁ በማለት፥ ይህን አጭር መልእክት ጽፌላችኋለሁ።