ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።
ዕብራውያን 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያን ትተውት የወጡትን አገር አስበው ቢሆን ኖሮ፥ ወደዚያ የመመለስ እድል በነበራቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትተዉት የወጡትን አገር ቢያስቡ ኖሮ፣ ወደዚያ የመመለስ ዕድል ነበራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያንን የወጡበትን አገር አስታውሰውት ቢሆኑ ኖሮ ወደዚያ ለመመለስ በቻሉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርስዋ የወጡባትን ሀገር ቢሹ ኖሮስ፥ ወደ እርስዋ ሊመለሱ በተቻላቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤ |
ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።