ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፥ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር።
ዘፍጥረት 41:55 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራቡ በመላው የግብጽ ምድር መስፋፋት ሲጀምር፥ ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፈርዖንም ግብፃውያኑን፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራቡ በመላው የግብጽ ምድር መስፋፋት ሲጀምር፣ ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፈርዖንም ግብጻውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራብ በመላው ግብጽ ምድር እየተስፋፋ በሄደ ጊዜ፥ ሕዝቡ ወደ ፈርዖን ሄዶ “ምግብ ስጠን!” ብሎ ጮኸ። ፈርዖንም “ወደ ዮሴፍ ሂዱና እርሱ የሚላችሁን አድርጉ” ብሎ አዘዛቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የግብፅ ምድርም ሁሉ ተራበ፤ ሕዝቡም ስለ እህል ወደ ፈርዖን ጮኸ፤ ፈርዖንም የግብፅ ሰዎችን ሁሉ፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግብፅ ምድርም ሁሉ ተራበ ሕዝቡም ስለ እህል ወደ ፈርዖን ጮኽ ፈርዖንም የግብፅ ሰዎችን ሁሉ፦ ወደ ዮሴፍ ሂዱ፥ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ አላቸው። |
ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፥ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር።
በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዥ ነበር፤ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደ ደረሱ፥ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው እጅ ነሡት።
እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።