ፈርዖንም ዮሴፍን “ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱጠ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ።
ዘፍጥረት 41:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት፥ የሄልዮቱ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት፣ የሄልዮቱ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባቱ የራብ ዓመቶች ከመጀመራቸው በፊት፥ ዮሴፍ ከጶጢፌራ ልጅ ከአስናት ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት። |
ፈርዖንም ዮሴፍን “ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱጠ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ።
አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፥ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።