ዘፍጥረት 41:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፥ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከሱትና አስከፊ የሆኑት ላሞች በመጀመሪያ የወጡትን ሰባት የወፈሩ ላሞች ዋጡአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያ የከሱትና መልከ ክፉዎቹ ላሞች እነዚያን የመጀመሪያዎቹን ያማሩና የወፈሩ ሰባት ላሞች ዋጡአቸው፤ በሆዳቸውም ተዋጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ላሞች የመጀመሪያዎቹን ወፍራሞቹን ስባት ላሞች ዋጡአቸው፥ |
ከእነርሱም በኋላ፥ ዐቅመ ደካማ፥ መልካቸው እጅግ የከፋና ዐጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብጽ ምድር ከቶ አይቼ አላውቅም።