La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 39:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ የወህኒው አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች ሁሉ አለቃ አደረገው፤ በእስር ቤቱ ላለውም ነገር ሁሉ ኀላፊ ሆነ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ የወህኒው አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች ሁሉ አለቃ አደረገው፤ በእስር ቤቱ ላለውም ነገር ሁሉ ኀላፊ ሆነ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ዐይነት በእስረኞቹ ሁሉ ላይና በእስር ቤቱ ውስጥ በሚደረገው ነገር ሁሉ ላይ ኀላፊ አደረገው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የግ​ዞት ቤቱም አለቃ በግ​ዞት ያሉ​ትን እስ​ረ​ኞች ሁሉ በዮ​ሴፍ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ በዚ​ያም የሚ​ደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በግዞት ቤቱም አለቃ በግዞት ያሉትን እስረኞች ሁሉ በዮሴፍ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው በዚያም የሚደረገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚያደርገው ነበረ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 39:22
8 Referencias Cruzadas  

ጌታውም ዮሴፍን ወስዶ፥ የንጉሥ እስረኞች ወደ ተጋዙበት እስር ቤት አስገባው።


ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፤ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፤ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኀላፊነት ሰጠው።


በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኀላፊነት ያለው ማንም የለም፤ እርሱ ያልሰጠኝ ነገር ቢኖር፥ አንቺን ብቻ ነው፤ ያውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ?”


ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።


በጌታ ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።