La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 37:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኛ ሁላችን በዕርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ በድንገት ተነሥታ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች ዙሪያዋን ከብበው ለእኔ ነዶ ሰገዱላት።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ የስንዴ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ እኛ በእ​ርሻ መካ​ከል ነዶ ስና​ስር ነበ​ርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእ​ና​ን​ተም ነዶ​ዎች በዙ​ርያ ከብ​በው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና እነሆም የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 37:7
12 Referencias Cruzadas  

አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”


እርሱም አላቸው፦ “እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፥


በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዥ ነበር፤ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደ ደረሱ፥ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው እጅ ነሡት።


በዚህ ጊዜ ስለ ወንድሞቹ ያየው ሕልም ትዝ አለውና፥ “ሰላዮች ናችሁ፤ የመጣችሁት አገራችን በየትኛው በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው።


ዮሴፍም ወደ ቤቱ ሲገባ ያመጧቸውን እጅ መንሻዎች አበረከቱለት፤ ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት።


እነርሱም መልሰው፥ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው በአክብሮት እጅ ነሡት።


ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ፥ እርሱ ገና ከቤቱ አልወጣም ነበር። እነርሱም ከፊቱ መሬት ላይ ተደፉ።


ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖን ያህል የተከበርህ ስለሆንህ፥ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ።


ጌታዬ ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ?’ ብሎ አገልጋዮቹን ጠይቈ ነበር።


ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው፦ “እነሆ እኛ ለአንተ ባርያዎችህ ነን አሉት።”


በዚህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም እንዲንበረከኩና


እርሱም አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር ቀዳሚ በመሆን መጀመሪያ ነው፤ ከሙታንም በኩር ነው።