በዚያም ቀን ከተባዕቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።
ዘፍጥረት 30:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱና በያዕቆብ መካከልም የሦስት ቀን መንገድ ያህል አራቃቸው፥ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን በጎች ይጠብቅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በርሱና በያዕቆብ መካከል የሦስት ቀን መንገድ ርቀት እንዲኖር አደረገ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጎች ማገዱን ቀጠለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ላባ መንጋውን ነድቶ የሦስት ቀን መንገድ ያኽል ከያዕቆብ ርቆ ሄደ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጋዎች መጠበቁን ቀጠለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱና በያዕቆብ መካከልም የሦስት ቀን መንገድ ያህል አራቃቸው፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን በጎች ይጠብቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱና በያዕቆብ መካከልም የሦስት ቀን መንገድ ያህል አራቃቸው፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን በጎች ይጠብቅ ነበር። |
በዚያም ቀን ከተባዕቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።
ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለውን ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው።