La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 2:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አዳምም አለ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ የተገኘች ናት፥ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ሴት ተብላ ትጠራ፥ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አዳምም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ‘ሴት’ ትባል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አዳምም፥ “እነሆ በመጨረሻ እርስዋ ከአጥንቶቼ የተገኘች አጥንት ናት፤ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥ​ንት ከአ​ጥ​ንቴ ናት፤ ሥጋ​ዋም ከሥ​ጋዬ ናት፤ እር​ስዋ ከባ​ልዋ ተገ​ኝ​ታ​ለ​ችና ሚስት ትሁ​ነኝ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አዳምም አለ፤ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 2:23
6 Referencias Cruzadas  

ላባም፦ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።”


እናንተ የዐጥንቴ ፍላጭ፥ የሥጋዬ ቁራጭ ወንድሞቼ ናችሁ፤ ታዲያ ንጉሡን ለመመለስ እንዴት የመጨረሻ ሰዎች ትሆናላችሁ?’


የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ፥ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤


“የሴኬምን ነዋሪዎች ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ጠይቋቸው፤ ‘ሰባዎቹ የይሩባኣል ልጆች ቢገዟችሁ ይሻላል ወይስ አንድ ሰው ብቻ?’ የሥጋችሁ ቁራጭ፥ ያጥንታችሁ ፍላጭ መሆኔን ልብ በሉ።”