ሕዝቅኤል 48:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መባው ሁሉ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ የተቀደሰውን መባ ከከተማይቱ ድርሻ ጋር አራት ማዕዘን አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አጠቃላይ ይዞታው በአራቱም ማእዘን እኩል ሲሆን፣ እያንዳንዱ ማእዘን ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከከተማዪቱ ድርሻ ጋራ የተቀደሰውን ክፍል ልዩ መባ በማድረግ ታስቀምጣላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም በምድሪቱ መኻል የተለየው ቅዱስ ድርሻ በጠቅላላው የእያንዳንዱ ማእዘን ርዝመት ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ሲሆን እርሱም ከተማይቱ የተሠራችበትን ቦታ ያጠቃልላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መባው ሁሉ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ፥ ወርዱም ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ የተቀደሰውን መባ ከከተማዪቱ ይዞታ ጋር አራት ማዕዘን አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መባው ሁሉ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ የተቀደሰውን መባ ከከተማይቱ ይዞታ ጋር አራት ማዕዘን አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ። |
በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ለአለቃው ይሆናል፤ በመባው በሃያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል በሀያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምዕራቡ ድንበር፥ እንደ ዕጣ ክፍሎች ሁሉ መጠን፥ ለአለቃው ይሆናል፤ የተቀደሰውም መባና ቤተ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።
ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፤ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት፤ ሁለት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ሜትር ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።