ሕዝቅኤል 46:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአደባባዩ በአራቱ ማዕዘን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ የታጠረ አደባባይ ነበረ፤ በአራቱም ማዕዘን ያሉት እኩል ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውጩ አደባባይ ባለው በአራቱ ማእዘን የታጠሩ አደባባዮች አሉ፤ ርዝመታቸው አርባ ክንድ፣ ወርዳቸውም ሠላሳ ክንድ ነበር፤ በአራቱም ማእዘን ያሉት አደባባዮች እኩል ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራቱ ማእዘኖች ያሉት ትናንሽ አደባባዮች እኩል ነበሩ፤ እያንዳንዳቸውም አርባ ክንድ ርዝመትና ሠላሳ ክንድ ወርድ ነበራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአደባባዩ በአራቱ ማዕዘን ርዝመቱ አርባ ክንድ፥ ወርዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ የታጠረ አደባባይ ነበረ፤ በማዕዘኑ ላሉ ለእነዚህ ለአራቱ ስፍራዎች አንድ ልክ ነበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአደባባዩ በአራቱ ማዕዘን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ የታጠረ አደባባይ ነበረ፥ በማዕዘኑ ላሉ ለእነዚህ ለአራቱ ስፍራዎች አንድ ልክ ነበረ። |