ሕዝቅኤል 42:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውጭው አደባባይ በኩል የነበሩት ክፍሎች ርዝመታቸው አምሳ ክንድ ሲሆን በመቅደሱ ፊት ለፊት የነበሩት ክፍሎች ግን ርዝመታቸው መቶ ክንድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከውጩ አደባባይ ቀጥሎ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ዐምሳ ክንድ ሲሆን፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውጪው አደባባይ በኩል ያሉት ክፍሎች ኀምሳ ክንድ ርዝመት ሲኖራቸው ከቤተ መቅደሱ ትይዩ ያሉት ክፍሎች ግን መቶ ክንድ ርዝመት ነበራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅደሱ ፊት የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው መቶ ክንድ ሲሆን፥ በውጭው አደባባይ በኩል የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው አምሳ ክንድ ነበረና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅደሱ ፊት የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው መቶ ክንድ ሲሆን በውጭው አደባባይ በኩል የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው አምሳ ክንድ ነበረና። |