ሕዝቅኤል 41:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጓዳዎቹም የውጭው ግንብ ውፍረት አምስት ክንድ ነበረ፤ በቤቱ ጓዳዎች አጠገብ የቀረ ባዶ ስፍራ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውጭ በኩል ያለው የግራና የቀኙ ክፍሎች ግንብ ውፍረት ዐምስት ክንድ ነበር፤ ክፍቱ ቦታ በቤተ መቅደሱና አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የውጪው ክፍሎች ግድግዳ ውፍረት አምስት ክንድ ነበር፤ ከቤተ መቅደሱ ጐን ካሉት ክፍሎችና ከሚቀጥሉት ሕንጻዎች መካከል ባዶ ቦታ ነበር፤ የዚህም ባዶ ቦታ ስፋት በሃያ ክንድ ቤተ መቅደሱን ይዞር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጓዳዎቹም የውጭው ግንብ ወርድ አምስት ክንድ ነበረ፤ በመቅደሱም ጓዳዎች አጠገብ የቀረ አንድ ባዶ ስፍራ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጓዳዎቹም የውጭው ግንብ ውፍረት አምስት ክንድ ነበረ፥ በመቅደሱም ጓዳዎች አጠገብ የቀረ አንድ ባዶ ስፍራ ነበረ። |
በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጪው አደባባይ አወጣኝ፥ በተለየው ስፍራ ፊት ለፊት፥ በሰሜን በኩል ባለው ህንጻ ፊት ለፊት ወዳለው ክፍል አገባኝ።