ሕዝቅኤል 41:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጓዳዎቹም መግቢያ በባዶው ስፍራ አንዱ በሰሜን በኩል አንዱም በደቡብ በኩል ነበረ፤ የባዶውም ስፍራ ወርድ ዙሪያው አምስት ክንድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከክፍቱ ቦታ ግራና ቀኝ ወዳሉ ክፍሎች የሚያስገቡ በሮች ነበሩ። አንዱ በሰሜን በኩል ሲሆን፣ ሌላው በር ደግሞ በደቡብ በኩል ነው። ክፍቱን ቦታ ዙሪያውን የሚያገናኘው መሠረት ስፋቱ ዐምስት ክንድ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደሱ ጐን ያሉት ክፍሎች በሮቻቸው የሚከፈቱት ወደ ባዶው ቦታ አቅጣጫ ሲሆን አንዱ በሰሜን በኩል ሌላው ደግሞ በደቡብ በኩል ይከፈታል፤ የተተወውም ባዶ ቦታ ዙሪያው አምስት ክንድ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጓዳዎቹም መግቢያ ብቻውን ወደሚኖረው ስፍራ ነበረ፤ አንዱ ደጅ ወደ ሰሜን መንገድ፤ አንዱም ደጅ ወደ ደቡብ መንገድ፥ ብቻውን የሚኖረው ስፍራ ወርዱ አምስት ክንድ በዙሪያው ነበር። |