ሕዝቅኤል 34:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም በጎቼ፥ የማሰማርያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ እኔም አምላካችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በጎቼ የማሰማሪያዬ በጎች ያልኋችሁ፣ ሕዝብ ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በበጎች የተመሰላችሁትና እኔ የማሰማራችሁ መንጋ እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም በጎች፥ የማሰማሪያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም በጎቼ፥ የማሰማርያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ እኔም አምላካችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። |
እንደ ተቀደሰ መንጋ፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም መንጋ፥ እንዲሁም የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
በአትክልት ቦታ መካከል ባለው ጥሻ ብቻቸውን የተቀመጡት የርስትህን መንጋ፥ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀደመው ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።