ሕዝቅኤል 16:58 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፋትሽንና ርኩሰነትሽን መሸከም አለብሽ፥ ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለብልግናሽና ለአስጸያፊ ተግባርሽ የሚገባውን ቅጣት ትሸከሚያለሽ፤ ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስድነትሽ በአጸያፊ ተግባርሽ ቅጣትሽን መቀበል አለብሽ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአትሽንና በደልሽን ተሽክመሻል፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምንዝርነትሽንና ርኵሰነትሽን ተሸክመሻል፥ ይላል እግዚአብሔር። |
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ አስቆጣሽኝ እንጂ የልጅነትሽን ወራት አላስታወስሺም፤ ስለዚህ እነሆ እኔ ደግሞ መንገድሽን በራስሽ ላይ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በርኩሰቶችሽ ሁሉ ላይ ሌላ ነውር አትጨምሪም።