ዘፀአት 40:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ፥ ወደ መሠዊያውም በሚቀርቡበት ጊዜ ይታጠቡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡና ወደ መሠዊያው በቀረቡ ቍጥር ይታጠቡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ድንኳኑ በሚገቡበትና ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ይህን ማድረግ ነበረባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ወደ ምስክሩ ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ወደ መሠዊያውም በቀረቡ ጊዜ ይታጠቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ወደ መሠዊያውም በቀረቡ ጊዜ ይታጠቡ ነበር። |