ዘፀአት 40:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመታጠቢያውን ሳሕን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀመጠ፥ ለመታጠቢያም ውኃን ጨመረበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመታጠቢያውን ሰን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀመጠ፤ ለመታጠቢያም ውሃ አደረገበት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመታጠቢያውንም ሳሕን በድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አስቀምጦ ውሃ ሞላበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመታጠቢያውንም ሰን በምስክሩ ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አኖረ፤ ለመታጠቢያም ውኃን ጨመረበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የመታጠቢያውን ሰን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አኖረ፥ ለመታጠቢያም ውኃን ጨመረበት። |
ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን በማደሪያው መግቢያ ፊት አኖረ፥ የሚቃጠልና የእህልን መሥዋዕት ሠዋበት።