La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 40:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴ ማደሪያውን ተከለ፥ እግሮቹን አኖረ፥ ሳንቆቹን አቆመ፥ መወርወሪያዎቹን አደረገባቸው፥ ምሰሶቹንም አቆመ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴ የማደሪያውን ድንኳን በተከለ ጊዜ፣ መቆሚያዎቹን በቦታቸው አኖረ፤ ወጋግራዎቹን አቆመ፤ አግዳሚዎቹን አስገባ፤ ምሰሶዎቹንም ተከለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴ ድንኳኑን ተከለ፤ የድንኳኑን እግሮች አኖረ፤ ተራዳዎቹንና ምሰሶዎቹን አቆመ፤ መወርወሪያዎቹንም አያያዘ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም ድን​ኳ​ን​ዋን ተከለ፤ እግ​ሮ​ች​ዋ​ንም አኖረ፤ ሳን​ቆ​ች​ዋ​ንም አቆመ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋ​ንም አቆመ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም እንዳዘዘው ሙሴ ማደሪያውን ተከለ፥ እግሮቹንም አኖረ፥ ሳንቆቹንም አቆመ፥ መወርወሪያዎቹንም አደረገባቸው፥ ምሰሶቹንም አቆመ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 40:18
15 Referencias Cruzadas  

እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ ድንኳንን ማደሪያዬ አድርጌ ከቦታ ወደ ቦታ ተጓዝሁ እንጂ በቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም


እንዲህም ሆነ፤ በሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ማደሪያው ተተከለ።


ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ድንኳኑን በማደሪያው ላይ ዘረጋ፥ የድንኳኑንም መደረቢያ በላዩ አደረገበት።


“በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ማደሪያ ትተክላለህ።


በዚያም የሚኖር ማንም፦ “ታምሜአለሁ” አይልም፤ በእርሷም ለሚኖሩ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።


ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ፤ ነፍሴም አትጸየፋችሁም።


እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይነግሱባትም።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በእኛም ዘንድ አደረ፤ ጸጋንና እውነትን የተመላውን፥ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብሩንም አየን።


የዘመኑ ሙላት በመጣ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ፤


ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።


ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ተዘጋጅቶላችኋል።


ታላቅም ድምፅ ከሰማይ ከዙፋኑ ወጥቶ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤