ዘፀአት 40:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንንና ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ታቀርባቸዋለህ፥ በውኃም ታጥባቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ አምጥተህ በውሃ ዕጠባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮንንና ልጆቹን ወደ ድንኳን ደጃፍ አምጥተህ እንዲታጠቡ አድርጋቸው፤ እጠባቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንንና ልጆቹንም ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አቅርበህ በውኃ ታጥባቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አቅርበህ በውኃ ታጥባቸዋለህ። |
ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ ከውኃ ወጣ፤ እነሆ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየ፤
መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።