ዘፀአት 38:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሸከሙትም መሎጊያዎቹን በመሠዊያው ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባ፤ ክፍትም አድርጎ ከሳንቃዎች ሠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጐኖች ይሆኑ ዘንድ መሎጊያዎቹን በቀለበቶቹ ውስጥ አስገቧቸው፤ ውስጡንም ክፍት በማድረግ ከሳንቃዎች ሠሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመሠዊያው ጐንና ጐን ባሉት ቀለበቶችም ውስጥ አስገባቸው፤ መሠዊያው ከሳንቃ የተሠራ ሆኖ ውስጡ ክፍት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሸከሙባቸውም ዘንድ በመሠዊያው ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አገባ፤ ከሳንቃዎቹም ሠርቶ ክፍት አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሸከሙትም ዘንድ በመሠዊያ ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አገባ፤ ከሳንቆቹም ሠርቶ ባዶ አደረገው። |