La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 38:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ምሰሶዎቹ አራት ነበሩ፤ ከነሐስ የተሠሩ እግሮች አራት፥ ኩላቦቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ፥ ጉልላቶቻቸውና ዘንጎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ነበሩት፤ ኵላቦቻቸውና ዘንጎቻቸው የብር ሲሆኑ፣ ጫፎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አራት የነሐስ እግሮች ባሉአቸው አራት ምሰሶዎች ተደግፎ ነበር፤ ኩላቦቻቸው፥ ጫፎቻቸውና ዘንጎቻቸው ከብር የተሠሩ ነበሩ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከናስ የተ​ሠሩ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ነበሩ፤ ኵላ​ቦ​ቹም የብር ነበሩ፤ ጕል​ላ​ቶ​ቹና ዘን​ጎ​ቹም በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከናስ የተሠሩ ምሰሶቹም አራት፥ እግሮቹም አራት ነበሩ፤ ኩላቦቹ የብር ነበሩ፤ ጉልላቶቹና ዘንጎቹም በብር ተለብጠው ነበር።

Ver Capítulo



ዘፀአት 38:19
4 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም በምሰሶዎቹ ላይ የሚቆሙ የእያንዳንዳቸው ቁመት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የሆነ ሁለት የነሐስ ጉልላቶችን ሠራ።


ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ።


የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተጠለፈ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች አምስት ክንድ ነበረ፤


የማደሪያውና በዙሪያው ያለ የአደባባዩ ካስማዎች ሁሉ ከነሐስ የተሠሩ ነበሩ።