የእስራኤል ልጆች የሙሴ ፊት እንዳንጸባረቀ ያዩ ነበር፤ ሙሴም ከእርሱ ጋር ለመነጋገር በፊቱ እስኪገባ ድረስ እንደገና በፊቱ ላይ መሸፈኛ ያደርግ ነበር።
ዘፀአት 34:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ጌታ በገባ ጊዜ፥ እስኪ ወጣ ድረስ መሸፈኛውን አነሣ፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ከርሱ ጋራ ለመነጋገር ወደ እግዚአብሔር ሀልዎት በሚገባበት ጊዜ ሁሉ ግን፣ እስከሚወጣ ድረስ መሸፈኛውን ያነሣ ነበር፤ በወጣም ጊዜ የታዘዘውን ለእስራኤላውያን ነገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ እግዚአብሔር መገኛ ድንኳን በገባ ቊጥር ሻሹን ከፊቱ ላይ ያነሣ ነበር፤ ከዚያም በሚወጣበት ጊዜ የታዘዘውን ሁሉ ለእስራኤላውያን ይነግራቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ከእርሱ ጋር ይነጋገር ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በገባ ጊዜ እስኪወጣ ድረስ መሸፈኛውን ከፊቱ ያነሣ ነበር፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ይነግራቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ከእርሱ ጋር ሲነጋገር ወደ እግዚአብሔር በገባ ጊዜ እስኪ ወጣ ድረስ መሸፈኛውን ከፊቱ አነሣ፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ነገረ። |
የእስራኤል ልጆች የሙሴ ፊት እንዳንጸባረቀ ያዩ ነበር፤ ሙሴም ከእርሱ ጋር ለመነጋገር በፊቱ እስኪገባ ድረስ እንደገና በፊቱ ላይ መሸፈኛ ያደርግ ነበር።