ለአደባባዩም መግቢያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ የተጠለፈ ሀያ ክንድ መጋረጃ ይሁን፤ ምሰሶዎቹ አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ።
ዘፀአት 27:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአደባባዩም ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ይያያዙ፥ ኩላቦቻቸው ከብር እግሮቻቸው ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ ኵላቦችና የንሓስ መቆሚያዎች ይኑሯቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ዘንጎች ይያያዙ፤ ኲላቦቻቸው ከብር፥ እግሮቻቸውም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያውም ያሉ የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ በብር የተለበጡ ይሁኑ፤ የብርም ክባሶች፥ የናስም እግሮች ይሁኑላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአደባባዩም ዙሪያ ላሉት ምሰሶች ሁሉ የብር ዘንጎች፥ የብርም ኩላቦች፥ የናስም እግሮች ይሁኑላቸው። |
ለአደባባዩም መግቢያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ የተጠለፈ ሀያ ክንድ መጋረጃ ይሁን፤ ምሰሶዎቹ አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ።
የአደባባዩ ርዝመት መቶ ክንድ፥ ስፋቱ አምሳ ክንድ ይሁን፥ ከፍታው አምስት ክንድ ይሁን፥ መጋረጃውም ከጥሩ በፍታ፥ እግሮቹም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።